BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በመንግሥት ብቻ በነጻ ይሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በክፍያ ሊሆን ነው
መንግሥት ለተጠቃሚዎች በነጻ ይሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በክፍያ እንዲሆን እና የግል ዘርፍ ተዋንያን እንዲሳተፉበት የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 19/2017 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ "ባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር" አዋጅ ይሰኛል።
ቡና መጠጣት ለጤና ጠቃሚ ነው ጎጂ? በምን ያህል መጠን?
ቀደም ባሉት ጊዜያት ቡና ከጤና እክሎች ጋር ተያይዞ ስሙ በክፉ ይነሳ ነበር። ነገር ግን ባለፉት አስርት ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቡና መጠጣት ለጤና በረከት ሊሆን ይችላል። ሰዎች ለዘመናት ተፈጥሯዊ የካፌይን ምንጭ የሆነውን ቡና ሲጠጡ ቢቆዩም በጤና ላይ አለው ተብሎ ከሚናፈሰው አሉታዊ ወሬ ጋር ተያይዞ ለአስርት ዓመታት እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ መልዕክቶች ሲተላለፉ ቆይተዋል።
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ፣ቫግነር በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ከአገሪቱ ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ።
አሜሪካ ወደ ኤል ሳልቫዶር አባራው የነበረውን ግለሰብ ወደ አገር መልሳ ከሰሰች
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስህተት ከአገር ተባሯል በሚል የትራምፕ አስተዳደር እንዲመልሰው ሲጠይቀው የነበረው የኤል ሳልቫዶር ተወላጅ ክስ ተመሰረተበት። አሜሪካ በስህተት ወደ ኤል ሳልቫዶር ያባረረችውን ይህንን ግለሰብ ወደ አገር መልሳ በሁለት የፌደራል ወንጀሎች ክስ እንደመሰረተችበት ገልጻለች።
በዩኬ በሕገ ወጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች እስር መበራከቱ ተገለጸ
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንዳመለከቱት በዚህ ዓመት እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ ወደ 44 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩኬ የገቡ ሲሆን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የገቡት በአነስተኛ ጀልባዎች በሚደረግ ሕገ ወጥ ጉዞ ነው።
ሦስት ልጆቹን በመግደል የተከሰሰው አሜሪካዊ በፖሊስ እየተፈለገ ነው
ፔቲይን፣ ኢቭንሊ እና ኦሊቪያ የተባሉት ታዳጊዎቹ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ራቅ ባለ ሥፍራ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ታፍነው መሞታቸውን ፖሊስ ገልጿል።
"በሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለማጥናት 200 ሺህ ዶላር አሰባስቤያለሁ" የትራምፕ ፖሊሲ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታት አፍሪካዊት
ፋጡ ውሬ፣ ቤተሰቦቿ እና ወዳጆቿ በአሜሪካ ውስጥ ስመ ጥር በሚባለው ሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርቷ ለመክፈል 200 ሺህ ዶላር አሰባስበዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድገት ሳይሆን 'ሚራክል' ነው ያለው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው "ዕድገት ሳይሆን ሚራክል [ተዓምር] ነው" ሲሉ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች ላይ በተናገሩበት ቃለ ምልልሳቸው የሠራተኞች የደመወዝ ጥያቄን አንስተዋል።
በሐጅ ጉዞ ወቅት ምዕመናን ጤናማ ሆነው ለመቆየት የሚጠቅሙ ምክሮች
በባለፈው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ቢያንስ 1300 ሰዎች መሞታቸውን ሳዑዲ አረቢያ አስታውቃለች። አብዛኞቹም ሕይወታቸው ያለፈው በከፍተኛ ሙቀት ረጅም ርቀት ከተጓዙ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ቢል ጌትስ ካለው 200 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ውስጥ አብዛኛውን ለአፍሪካ ሊሰጥ መሆኑን በአዲስ አበባ ቆይታው ተናገረ
የማይክሮሶፍት መስራች ቢልጌትስ፤ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ካለው ሀብት ውስጥ አብዛኛውን በአፍሪካ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደሚያውል ተናገረ።ቢል ጌትስ በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው ንግግር አፍሪካውያን ወጣት ፈጣሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን (AI) በምን አይነት መንገድ በመጠቀም በአህጉራቸው የጤና አገልግሎትን ማሻሻል እንደሚችሉ እንዲያስቡ አሳስቧል።
ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ በሚያደርጉት ድብቅ ጦርነት ኪም ጆንግ ኡን እያሸነፉ ነው?
ደቡብ እና ሰሜን ኮሪያን የሚለየው አጥር የኤሌክትሪክ ገመድ አለው። ይህን አጥር የሚጠብቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችም ተደርድረዋል።
'የራሳቸውን ሕዝብ በፍርሃት የሸበቡ . . . ስለኢትዮጵያ ማውራት ባህሪያቸው ነው' - የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ 'እየተገነባ ያለው ሠራዊት ለትናንሽ ኃይሎች የተደራጀ አይደለም' ብለዋል። የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ ቅዳሜ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በተላለፈ ቃለ መጠይቅ ላይ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ምላሽ የሚመስል ትችት አንስተዋል። ፕሬዝደንት ኢሳያሳ ባለፈው ሳምንት ባሰሙት ንግግር የኢትዮጵያ መንግሥት በፅኑ መተቸታቸው ይታወሳል። ሚኒስትሯ በቃለ-ምልልሳቸው ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ?
የጤና ባለሙያዎች ከመንግሥት ጋር ምን ተነጋገሩ? በሦስተኛ ወገን ለመነጋገር የተጀመረው ጥረት ምንድን ነው?
የደሞዝ፣ የጥቅማ ጥቅም እንዲሁም ሌሎች ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ በመጠየቅ የሥራ ማቆም አድማ ከመቱ ሦስት ሳምንታት የሆናቸው የጤና ባለሙያዎች ግንቦት 15/2017 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የሥራ ማቆም አድማ በኢትዮጵያ ከትላንት እስከ ዛሬ . . .
የኢትዮጵያ ሠራተኞች መደራጀት፣ የተሻለ ደመወዝ፥ የሥራ እና የኑሮ ሁኔታዎችን እንዲመቻቹላቸው መጠየቅ ከጀመሩ ስድስት አስርት ዓመታትን አስቆጥረዋል። በእነዚህ ዓመታት ጥያቄዎቻቸው ጆሮ እንዲያገኙ ከሥራ ማቆም አድማ ጀምሮ የአደባባይ ተቃውሞ እስከ ማድረግ የደረሱ የትግል ስልቶችን ተጠቅመዋል። ነገር ግን እነዚህ የሥራ ማቆም አድማዎች ምን አስገኙ? ምንስ ገጠማቸው?
ሩሲያን ድል እያቀዳጀ ያለው 'ፋይበር ኦፕቲክ' ድሮን
የፋይበር ኦብቲክ' ድሮን 'ጭራ' ላይ በ10 ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ ገመድ ይጠመጠምባቸዋል። በሌላኛ ጫፍ ድግሞ ድሮኑን ከሚቆጣጠረው መሳሪያ ጋር ይገናኛሉ። "ወደ ድሮኑ የሚመጣውም ይሁን ከድሮኑ የሚወጣው ቪዲዮና የቁጥጥር ሲግናል የሚተላለፈው በኤሌክትሪክ ገመዱ (ኬብል) አማካኝነት እንጂ እንደሌላው ድሮን በሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ አይደለም። ይህ ማለት በኤሌክትሮኒክ የመከላከያ ሥርዓት የድሮኑን ጉዞ ማጨናገፍ አይቻልም ማለት ነው" ሲል አንድ የዩክሬን ድሮን ማሃንዲስ ነግሮናል።
ከየፈርጁ
ለአእምሮ ጤና እና ደስተኛ ለመሆን የሚያግዙ አራት መንገዶች
ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ ሰውነትዎ ዶፓሚን፣ ኦክሲቶሲን፣ ሴሮቶኒን እና ኢንዶርፊን የተባሉትን አራት ሁነኛ ሆርሞኖች ይፈልጋል።ሁሉም ሰው በሕይወት ዘመኑ የሆነ ወቅት ላይ ከአእምሮ ጤና ጋር ችግር መግጠሙ አይቀርም። ነገር ግን የሰውነትን ኬሚስትሪ ሚዛን ለመጠበቅ እና ደኅንነትን ለመጠበቅ ሊደረጉ የሚችሉ ትናንሽ፣ ነገር ግን ተግባራዊ እርምጃዎች አሉ።
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ስለሚጫወቱ ምርጥ አፍሪካዊያን ከዋክብት ቁጥሮች ምን ይላሉ?
የአውሮፓውያኑ 2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ውድድር በሊቨርፑል አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህ የውድድር ወቅት በርካታ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ለተለያዩ ቡድኖች ተሰልፈው ትኩረትን ስበዋል። እነዚህ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ደምቀው የታዩ አፍሪካውያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው?
ከእርግዝና ውጪ የወር አበባ እንዲቀር የሚያደርጉ ስምንት ምክንያቶች
የወር አበባ መቅረት (amenorrhea) በብዛት ከእርግዝና ጋር ይተሳሰራል። ሆኖም ግን እርግዝና ሳይፈጠርም የወር አበባ የሚቀርባቸው ምክንያቶች አሉ። የወር አበባ አልፎ አልፎ ቢቀር እንደ ችግር ባይወሰድም በተደጋጋሚ ከተከሰተ መነሻ ምክንያቱ መታወቅ አለበት።
ዓለማት ለምን እና እንዴት እንደተፈጠሩ ለማወቅ እየጣሩ ያሉት የ30 አገራት ሳይንቲስቶች
የሰው ልጅ ምድር በምትባለው ፕላኔት ላይ መኖር ከመጀመሩ በፊት የሆነው ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከ30 አገራት ሳይንቲስቶች ተሰባስበዋል። በአሜሪካ በሚገኝ አንድ ቤተ ሙከራ ውስጥ የሳይንስ ሊቃውንት ለአንድ ትልቅ ሳይንሳዊ ጥያቄ መልስ እየፈለጉ ነው። ጥያቄው አጽናፈ ዓለማት ወይንም ዩኒቨርስ ለምን ተፈጠሩ?
ኤአይ ያፈቅራል? ያዝናል? የኅልውና ስጋት ነው?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት በሰው ልጆች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖረው እንደሚችል እየተነገረ ነው። በተጨማሪም ‘ሰዋዊ’ ሊባሉ የሚችሉ ድርጊቶች ሊከውንም ይችላል እየተባ ሲሆን፣ አንዳንዶች ለሰው ልጆች ህልውና ስጋት ነው ይላሉ። ዕለት ከዕለት እየተራቀቀ የመጣው ሰው ሠራሽ አስተውሎት ማፍቀር እና ማዘንን የመሳሰሉ የሰው ልጆች ውስጥ የሚፈጠሩ ስሜቶችን ሊያሳይ ወይም ሊላበስ ይችላል?
የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ በኢትዮጵያ ሕጎች እንዴት ይታያል?
የደሞዝ እና ሌሎች የሥራ ሁኔታቸው እንዲሻሻል በመጠየቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ድርጊቱን የተቃወሙ የጤና ባለሥልጣናት ማስጠንቀቂያ ከመስጠታቸው ባሻገር፤ በርካታ የጤና ባለሙያዎች በፀጥታ ኃይሎች ታስረዋል። ይህ የጤና ባለሙያዎች የሥራ የማቆም አድማ በኢትዮጵያ ሕጎች እንዴት ነው የሚታየው?
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
ይህ ከ40ዎቹ የዕድሜ ክልል በተሻገሩ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የካንሰር ዓይነት በተመለከተ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች እዚህ ቀርበዋል። የፕሮስቴት ካንሰር ምንድን ነው? ማን የበለጠ ተጋላጭ ነው? መከላከል ይቻላል? መልክቶቹ ምንድን ናቸው? ሕክምናስ አለው?
አጃኢብ!
ለልጆቻችን ዕድገት እና የአእምሮ ጤና ጠቃሚ መሆኑ እየተነገረለት ያለው ንጥረ ነገር
ኮሊን የተባለው ንጥረ ነገር ለሰውነት ጠቃሚ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳል። ኮሊን የሰው ልጆች አእምሮ በአግባቡ እንዲሠራ ይረዳል። የማሰላሰል ብቃትን በማሻሻል ከአእምሮ ዕድገት ጋር የተያያዙ ህመሞችን በመከላከልም እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ።
ደንበኞች የሚፈልጉትን አንስተው በታማኝነት ከፍለው የሚገለገሉበት ጠባቂ አልባ ሱቆች
በእኩለ ሌሊት የሚቀመስ ነገር ለሻተ በደቡብ ኮሪያ መዲና ሴዑል የሚገኙ ሱቆች በሮቻቸውን ክፍት አድርገው ይጠብቃሉ። እነዚህ ሱቆች 24 ሰዓት ነው የሚያገለግሉት። ነገር ግን ሱቆችን የሚጠብቅም ሆነ ገንዘብ የሚቀበል ሰው የለም። ሰዎች ወደ ሱቆቹ ገብተው የፈለጉትን ካነሱ በኋላ በታማኝነት ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ከፍለው ይወጣሉ።
ቪዲዮ, ማክሮን በአደባባይ የተገፈተሩት 'ለቀልድ' እንጂ የቤት ውስጥ ጸብ አይደለም አሉ, ርዝመት 0,35
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጉብኝት ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የሆነው በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ፕሬዝዳንቱ ፊት ለፊት በሚታዩበት ጊዜ አንድ እጅ ጸብ በሚመስል ሁኔታ ፊታቸውን በኃይል ሲገፋ ታይቷል። በዚህ ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ምንም እንዳልተፈጠረ የእጅ ሰላምታ ሰጥተው ሚስታቸውን ከጎናቸው በማድረግ ከአውሮፕላኑ ወርደዋል።
ቱርክ አውሮፕላን ከመቆሙ በፊት የሚነሱ ተሳፋሪዎችን እቀጣለሁ አለች
ወደ ቱርክ የሚጓዙ መንገደኞች የአውሮፕላኑ የመቀመጫ ቀበቶ ምልክት ከመጥፋቱ በፊት ከተነሱ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተቆጣጣሪዎች ገለጹ።
ለውበት ሲባል የሚደረግ ቀዶ ሕክምና ፡ "100 የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና አድርጌያለሁ፤ ከዚህ በኋላም እቀጥላለሁ"
ከገቢ መጨመር እና የማኅበረሰባዊ አስተሳሰብ መለወጥ ጋር በተያያዘ በአንድ ወቅት እምብዛም የማይደገፈው የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ባለፉት 20 ዓመታት በቻይና እየተለመደ መጥቷል። 80 በመቶ ታካሚዎች ሴት ሲሆኑ፣ ዕድሜያቸው በአማካይ 25 ይደርሳል። በቻይና ባህል ውበት ከፍ ያለ ዋጋ ቢኖረውም ቆንጆ ተብሎ የሚወሰደው መልክ እየተለወጠ መጥቷል።
"ወንዳወንድ ለመሆን" በሚል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እየተቀላቀሉ ያሉት አሜሪካዊያን ወጣቶች
ዋና መቀመጫውን ኒው ዮርክ ግዛት ያደረገው ከሩሲያ ውጭ የሚገኙ የሩሲያ አብያተ-ክርስትያናት ተቋም በአሜሪካ እየተስፋፋ ይገኛል። ለዚህም አብይ ምክንያቱ በርካታ አዳዲስ ተከታዮች ማፍራቱ ነው።ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ አባ ሙሴ 75 አዳዲስ ምዕመናን አጥምቀዋል።
በመቶ ሺዎች ያስገጠሙት ማይክሮቺፕ በሰውነትዎ ውስጥ እንዲቀበር ይፈቅዳሉ?
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቺፕ በሰው ሰውነት ውስጥ የተቀበረው እአአ በ1998 ነበር።ከዚያ ወዲህ ከጤና እንዲሁም ከግብይት ጋር በተያያዘ ማይክሮቺፕ ማስቀበር የሚመርጡ ሰዎች ቁጥር እየተበራከረ መጥቷል። ለመሆኑ ማይክሮቺፕ ምንድን ነው? ለምን አገልግሎት ይውላል? ለሰው ልጆች ስጋት ነው? ዓለምንስ እንዴት ይለውጣል?
የተመለሱ ጥያቄዎች
የጣራ እና ግድግዳ እርጥበት ለአስም እና ለካንሰር ሊያጋልጠን እንደሚችል ያውቃሉ?
በሻጋታ ምክንያት የሚከሰት ቶክሲን የተባለ መርዛማ ኬሚካል ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሲሆን፣ የመተንፈሻ አካላትን ከመጉዳቱም በላይ ለካንሰርም ሊያጋልጥ ይችላል ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ። የቤት ውስጥ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ሻጋታ ገዳይ መርዝ የማመንጨት ኃይል አለው።
"ራሴን ለማጥፋት ጫፍ ላይ ደርሼ ነበር፤ አሁን ግን ሌሎችን እረዳለሁ"
በዓለም የጤና ድርጅት መሠረት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከአምስት ሴቶች አንዷ ከወሊድ በኋላ የአእምሮ ጤና መታወክ፤ በዋነኛነት የመንፈስ ጭንቀት ያጋጥማታል። የሆርሞን ለውጦች እንዲሁም ስቃይ የበረታበት ወሊድ፣ ድህነት ወይም ሐዘን የመሳሰሉ ጭንቀቶች በእርግዝና ወቅት እና ከእርግዝና በኋላ በአእምሮ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለማችን ወረርሽኝ ይሆናል ብለው ለምን ሰጉ?
ተመራማሪዎች ለወራት በእርሻዎች ላይ እየተስፋፋ ያለው የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለም ወረርሽኝ ይሆናል በሚል የማስጠንቀቂያ ደወል እያሰሙ ነው። በሽታዎች እንዴት እንደሚጎለብቱ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ልብ ሳንለው ወደ ሰዎች በመዛመት ወረርሽኝ ይሆናል በማለት አስጠንቅቀዋል።
በዓለም ዙሪያ የኦቲዝም ክስተት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል? ወይስ ሌላ ምክንያት አለ?
ኦቲዝም ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እየታወቀ እንዲሁም ሰዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ነው። ይህ ግን ኦቲዝም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤም ፈጥሯል።
'ሁሉም ዘመድ በሆነባት' ገጠራማ መንደር የተገኘ ነርቭን የሚያጠቃ ያልተለመደ በሽታ
በዘረ መል ለውጥ (genetic mutation) ምክንያት የሚከሰተው ይህ በሽታ የነርቭ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ቀስ በቀስ ሰውነትን ያዳክማል። በሽታው የሚከሰተው የተለወጠው ጂን ከሁለቱም ወላጆች ሲወረስ ብቻ ነው።
የውሃ ኮዳችን ለበሽታ እንደሚያጋልጠን ልብ ብለዋል? እንዴት ማፅዳት አለብን? ምን ዓይነት ኮዳ እንጠቀም?
ከኮዳዎ ውሃ በተጎነጩ ቁጥር ወደ ውስጡ ባክቴሪያዎችን እያስገቡ እንደሆነ ያውቃሉ? ሥራ ቦታ፣ ስፖርት ቤት አሊያም በየዕለት እንቅስቃሴያችን የምንገለገልባቸው የውሃ ኮዳዎች ለጤና ቀውስ ሊዳርጉን ይችላሉ። ይህንን አስቀድሞ ለመከላከል ምን ማድረግ እንደሚገባ ተመራማሪዎች የሰጡትን ምክር እናካፍላችሁ።
አልኮል መጠጥ በጤናችን እና በዕድሜያችን ላይ የሚያስከትለው ጉድለት
የአልኮል መጠጦች ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ይጠጣል፤ የብዙ ድግሶች ማድመቂያ ተደርጎም ይወሰዳል። ሰውነትን ስለሚያፍታታ በቀላሉ ከሰዎች ጋር ለማውራት የሚጠቀሙበትም ሰዎች አሉ። ሲደሰቱ፣ ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ሲቀላቀሉ ወይም ሲያዝኑም ወደ መጠጥ ፊታቸውን የሚያዞሩ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ባለሙያዎች በየትኛውም መጠን የሚጠጣ አልኮል በጤና እና በዕድሜ ላይ ዳፋ አለው ይላሉ።
በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት ሁሉ ኪንታሮት ነው? ኪንታሮት ካልታከመ ምን ያስከትላል?
የፊንጢጣ ኪንታሮት ሰዎች ብዙም የማይነጋገሩበት ህመም ነው። አንዳንዶች ሐኪም ለማማከርም ሲያመነቱ ይስተዋላል። ለመሆኑ በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት እና ህመም ሁሉ ኪንታሮት ነው? ሕክምና የሚያስፈልገውስ መቼ ነው? ካልታከመስ ምን ያስከትላል?
ሌላ ዕይታ
ከማኅደራችን
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከበሮ እና ጽናጽልን ሌሎች ቤተ እምነቶች እንዳይጠቀሙ መከልከል ትችላለች?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከበሮ፣ ጽናጽል እና መቋሚያ ንድፎችን በአዕምሯዊ ንብረትነት ማስመዝገቧን ተከትሎ ጉዳዩ ሲያከራክር ሰንብቷል። ምዝገባው ሌሎች ቤተ እምነቶች እነዚህን መገልገያዎች “እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት ይሰጣል ወይስ አይሰጥም?” የሚለው የክርክሩ ማጠንጠኛ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎች ያላቸው አረዳድ እና የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን አቋም የተለያየ ነው።
ዕድገት በኅብረት ዘመቻ፡ የሦስቱ ጓደኛሞች የ50 ዓመታት ትዝታ
ወታደራዊው አስተዳደር ደርግ የአገሪቱን የመሪነት መንበር ከያዘ በኋላ የዛሬ 50 ዓመት የዕድገት በኅብረት ዘመቻን አወጀ። በዚህም ከ10ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች እና መምህራን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተሰማርተው በማስተማር እና በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ አድርጎ ነበር። በዚህ ዘመቻ የተሳተፉ የዚያ ዘመን አፍላ ወጣቶች ከአምስት አሥርታት በኋላ በጋራ ተሰባስበው ያሳለፉትን ጊዜ አስታውሰዋል። ትዝታቸውንም ለቢቢሲ አጋርተዋል. . .
የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
የኢየሱስ ስቅለት እና ሞት በሕክምና ባለሙያዎች ዓይን እንዴት ይተነተናል?
በአይሁዶች እና ሮማውያን ችሎት ወንጀለኛ ተብሎ የቆመው ኢየሱስ ክርስቶስ በጥፊ ተመትቷል፣ ተገርፏል፣ ተራቁቷል፣ የእሾህ አክሊል ተደፍቶበታል። ኢየሱስ ከተያዘበት እስከ አርብ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብዙ ደም ፈስሶታል። ተጠምቷል። ከዚያም ሞቷል። የሕክምና ባለሙያዎች ኢየሱስ የደረሰበትን እንግልት፣ ድብደባ እና ስቅላት ከሙያቸው አንጻር እንዲህ ተንትነውታል።
'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ክፉኛ አቁስላ፣ ማርካ ያከመችው የጁባላንዱ ፕሬዚዳንት ማዶቤ
"የብዙ ኢትዮጵያዊ ደም ነው የወሰደው። የኢትዮጵያ ደም ነው ያለህ እንለዋለን" ይህ በሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሁኑ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዚዳንት ማዶቤ በቀልድ መልኩ ጣል ያደርጉላቸው ነገር ነው። ይህ በቀልድ የተለወሰ መሪር እውነታ ነው። እውነታው የሶማሊያዋን ራስ ገዝ ጁባላንድን ላለፉት 12 ዓመታት ያስተዳደረው ማዶቤ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ጦር ክፉኛ ቆስሎ በአዲስ አበባ ህክምና አድርጓል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?